About የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ካውንስል አባላት የ2017 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የማለፊያ ውጤት 50% እንዲሆን በዛሬው እለት ወስነዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ካውንስል አባላት የ2017 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የማለፊያ ውጤት 50% እንዲሆን በዛሬው እለት ወስነዋል።

02nd July, 2025

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ካውንስል አባላት የ2017 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የማለፊያ ውጤት 50% እንዲሆን በዛሬው እለት ወስነዋል።

(ሰኔ 25/2017 ዓ.ም)  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሰረት በከተማ አስተዳደሩ የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከ2015 የትምህርት ዘመን ጀምሮ መሰጠቱን እንዲሁም በ2017 የትምህርት ዘመን ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመስራቱ  የተመዘገበው ውጤት አበራታች መሆኑን ተናግረዋል።

ዶክተር ዘላለም አያይዘውም በ2017 ዓ.ም የሒሳብና እንግሊዘኛ ትምህርትን ለማሻሻል ተግባራዊ የተደረገው ስትራቴጂ በተማሪዎች ውጤት መረጋገጡን በተጨማሪም የከተማ አስተዳደሩ በትምህርት ዘርፉ ላይ ባደረገው ትኩረት ውጤቱ መመዝገቡን ተናግረው ፈተናውን በአጭር ጊዜ በማረም ውጤቱ ይፋ እንዲሆን ቀን ከሌት ሲሰሩ ለቆዩ የፈተና ክፍል ባለሙያዎችና ሂደቱን ሲደግፉ ለነበሩ አመራሮች ምስጋና አቅርበዋል። 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዲናኦል ጫላ በበኩላቸው በከተማ አስተዳደሩ በ2017 ዓ.ም 79,034 ተማሪዎች ፈተናውን መውሰዳቸውን ገልጸዋል፡፡

.

Copyright © All rights reserved.