About የ2018 የትምህርት ዘመን መሪ እቅድ ከቢሮ ሰራተኞች ጋር ተገመገመ ::

የ2018 የትምህርት ዘመን መሪ እቅድ ከቢሮ ሰራተኞች ጋር ተገመገመ ::

24th June, 2025

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ቀደም ሲል በስትራቴጂክ እና ጠቅላላ ካውንስል ደረጃ የተገመገመውን የ2017 የመደበኛ እና የሪፎርም ስራዎች እቅድ አፈጻጸም እና የ2018 የትምህርት ዘመን መሪ እቅድን ከቢሮ ሰራተኞች ጋር ገመገመ::

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አማካሪና የዘርፉ አስተባባሪ ወ /ሮ አበበች ነጋሽ  በውይይቱ ላይ ባስተላለፉት መልእክት በትምህርት ዘመኑ ቁልፍና አበይት ተግባራት የታቀዱ ሥራዎች የላቀ ውጤት የታየባቸው መሆኑን አስታውሰዋል::  በተጨማሪም ቀደም ሲል በስትራቴጂክ እና ጠቅላላ ካውንስል ደረጃ የተገመገመውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ  የ2017 የመደበኛ እና የሪፎርም ስራዎች እቅድ አፈጻጸም እና የ2018 የትምህርት ዘመን መሪ እቅድን ከቢሮ ሰራተኞች ጋር መገምገም በማስፈለጉ መድረኩ መጠራቱን ገልጸዋል :: አያይዘውም የዉይይቱ ተሳታፊዎች የ2017  ትምህርት ዘመን አጠቃላይ ስራችንን በመገምገም ክፍተት የታየባቸውን በሙሉ አቅምና በበለጠ የስራ ተነሳሽነት ለመስራት የሚያስችሉ ገንቢና ግብዓት የሚሆኑ ሀሳቦች እንዲሰጡ ይጠበቃል ብለዋል::

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፅ /ቤት ኃላፊ አቶ ሲሳይ እንዳለ በበኩላቸው ያለፈው በጀት ዓመት አፈፃፀምና የቀጣይ እቅድ ላይ ውይይት መደረጉ ቢሮው ያለውን የአፈፃፀም አቅም የምናይበትና በቀጣይ ለሚኖረን ሥራ ራሳችንን የምናዘጋጅበት ይሆናል ብለዋል:: አክለውም የውይይቱ ተሳታፊዎች የሚሰጡትን እቅድ ማዳበሪያ ሀሳብ በማከል የተማሪ ውጤትን ለማሻሻል በበለጠ ትጋት ለመስራት ራሳችንን እናዘጋጅ ብለዋል ::

በውይይቱ የእቅድ በጀት ዝግጅት ክትትል ግምገማ ዳይሬክተር አቶ ጌታሁን ለማ የ2017 ትምህርት ዘመን ስትራቴጂክ እቅድ አፈጻጸምና የ2018 ትምህርት ዘመን ረቂቅ እቅድ አቅርበዋል:: በተያያዘም የሪፎርም አገልግሎት አሰጣጥ ድጋፍ ክትትልና ምዘና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፈንታሁን እያዩ የ2017 በጀት አመት የአገልግሎት አሰጣጥና መልካም አስተዳደር ስራዎች አፈጻጸም ሪፖርትና የ2018 በጀት አመት የቅንጅታዊ ስራዎች እቅድ አቅርበው በቀረቡትን ሪፖርቶች የሚያዳብሩ ፍሬ ሀሳቦች በተሳታፊዎች ተነስተው  ውይይት ተደርጎበታል ::

በእቅድ ግምገማው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጠቅላላ ሰራተኞች እና ስትራቴጂክ ካውንስል አባላት በተገኙበት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል ::

.

Copyright © All rights reserved.