በውይይቱ የክፍለከተማ የመምህራን እና የትምህርት አመራር ልማት ቡድን መሪዎች እንዲሁም የዳይሬክቶሬቱ ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን በመርሀግብሩ የ4ኛ ሩብ አመት አፈጻጸምን መሰረት ያደረገ የድጋፍና ክትትል ግብረ መልስ በቢሮ የመምህራን ልማት ባለሙያ በወይዘሮ ፍሬሕይወት አስፋ ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የመምህራን እና የትምህርት አመራር ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ አበራ ስራ ክፍሉ በየሩብ አመቱ በዘርፉ የተከናወኑ ተግባራትን ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመሆን ሲገመግም መቆየቱን ገልጸው የዛሬው ውይይት በበጀት አመቱ የተከናወኑ ተግባራትን በመገምገም በ2018ዓ.ም የተሻለ ስራ ለመስራት የሚያስችል መሆኑን አስታውቀዋል።
ዳይሬክተሩ አያይዘውም ስራ ክፍሉ የ4ኛ ሩብ አመት አፈጻጸምን መሰረት ያደረገ ድጋፍና ክትትል ማድረጉን ገልጸው የድጋፍና ክትትል ግብረመልሱን የጋራ በማድረግ በቀጣይ የተሻለ ስራ የሚሰራ መሆኑን አመላክተዋል።
በመርሀግብሩ በዘርፉ በ90 ቀናት በሚከናወኑ ተግባራት ዙሪያ ውይይት ከመካሄዱ ባሻገር በ2017 ዓ.ም የመምህራን ኦዲት ሪፖርትን የጋራ የማድረግና በ2018 ዓ.ም የመምህራን ፍላጎት ዙሪያ ውይይት ተደርጎ ቀጣይ አቅጣጫ ተቀምጧል።
.