የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በከተማ አስተዳደሩ የ2017 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን በውጤታማነት ለመስጠት ተማሪዎችን ኦላይን ፈተና ወደሚሰጥባቸው የመፈተኛ ጣቢያዎች በሰዓቱ እንዲደርሱና ፈተናዉን ሳጠናቅቁ እንዲመለሱ ለማድረግ የሚያስችል ውይይት የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ስትራቴጂክ ካውንስል አባላት ፣ የክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ሀላፊዎችና የክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ሀላፊዎች በተገኙበት አካሄዳል፡፡
በውይይቱ ላይ በከተማ አስተዳደሩ የሚሰጠው ብሔራዊ ፈተና ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲከናወን በየደረጃው የሚገኙ የጸጥታ መዋቅሩ አመራሮችና አባላት እያደረጉ ለሚገኘው የማይቋርጥ ድጋፍ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ምስጋና አቅርበው ዘንድሮ በአዲስ አበባ ከተማ ከዚህ በፊት ከነበረው አንጻር የ2017 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በኦላይን የሚሰጥ በመሆኑ ፈተና መስጫ ጣቢያዎች ላይ ተማሪዎች በሰዓቱ እንዲደርሱና ፈተናቸዉን ሳጠናቅቁ እንዲመለሱ ለማድረግ ተሸከርካሪ አቅራቢዎች የተገኙ መሆኑን ጠቅሰው በስራዉ ሂደት ላይ በመወያየት ከመግባባት ላይ መደረሱን ተናግረዋል፡፡
በኤች አይ ቪ ኤድስ ዙሪያ በየጊዜው በሚደረግ የማህበረሰብ ውይይት ግንዛቤ ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑን የተናገሩት የቢሮው ኤች አይ ቪ መከላከልና መቆጣጠር ባለሙያ አቶ ወርቁ በንታ ከቢሮው ባለሙያዎች ጀምሮ እስከታች ድረስ ያለውን የትምህርት አካላት ለማግኘት ከክበባት ጋር በመቀናጀት ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን ተናግረዋል:: ከዚህ ጋር በተያያዘ ቢሮው በተለያየ ጊዜ በስልጠናና መሰል የማህበረሰብ ውይይት የሚያደርገውን ግንዛቤ ችላ ሳይሉ ለሌሎችም በማስተማር ራሳቸውንና ማሀበረሰቡን ከበሽታው የመከላከል ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል ::
በስልጠናው የኤች አይቪ መሰረታዊ እውነታዎች እና ሜንስትሪሚንግ ላይ ትኩረት ያደረገ ሰነድ የጤና ባለሙያ በሆኑት አቶ ስንታየሁ ጎሹ አማካኝነት የቀረበና ውይይት የተደረገበት ሲሆን የቢሮው አጠቃላይ ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል ::
.