የሙከራ ፈተናውን በተለያዩ የመንግስትና የግል ትምህርት ቤት የሚማሩ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የወሰዱ ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ስትራቴጂክ ካውንስል አባላትና የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ አመራሮች ጋር በመሆን የሙከራ ፈተናው በተሰጠባቸው ጣቢያዎች በመገኝ ሂደቱን ተመልክተዋል።
በከተማ አስተዳደሩ በበይነ መረብ የሚሰጠው የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ስኬታማ እንዲሆን የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ የሚገኝ ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክብርት ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ሂደቱ ስኬታማ እንዲሆን የቅርብ ድጋፍና ክትትል በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
በዛሬው የሙከራ ፈተና ኮምፒውተሮች ፣ ታብሌቶች እንዲሁም ላፕቶፖች እና ሌሎች ለፈተናው የሚያስፈልጉ መሰረተ ልማቶቹ ዝግጁ መሆናቸውን ማረጋገጥ ተችሏል።
በከተማ አስተዳደሩ በዛሬው እለት በሁሉም የመፈተኛ ጣቢያዎች የተሰጠው የሙከራ ፈተና ስኬታማ ከመሆኑ ባሻገር ከሰኔ 23/2017ዓ.ም ጀምሮ ለሚሰጠው መደበኛው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተማሪዎቹ በአግባቡ እንዲዘጋጁ ምቹ ሁኔታ የተፈጠረበት መሆኑን በተለያዩ ጣቢያዎች የሙከራ ፈተናውን የወሰዱ ተማሪዎች አረጋግጠዋል።
.