የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን በበይነ መረብ ቀጥታ (online) የሚፈተኑ ተማሪዎች በተለያዩ የመፈተኛ ጣቢያዎች ለሁለት ቀናት ሳከናውኑት የቆየው ልምምድ በስኬት ተጠናቋል።
(ግንቦት 22/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ተፈታኝ ተማሪዎቹ ልምምድ ከሚያደርጉባቸው የፈተና ጣቢያዎች መካከል ከቢሮው ስትራቴጂክ ካውንስል አባላት ጋር በመሆን በተዘጋጁት የፈተና ጣቢያዎች ላይ ተማሪዎች ሳከናውናቸው የቆዩትን የፈተና ልምምዶች ተገኝተው ምልከታ አካሂደዋል።
ፈተናውን በበይነ መረብ የሚወስዱ ተማሪዎች ለሁለት ቀናት ያካሄዱት የሙከራ ፈተና በስኬት መጠናቀቁ ፤ በቀጣይም ተማሪዎች ከመደበኛው ፈተና በፊት ተመሳሳይ የሙከራ ፈተና እንደሚወስዱ እና ለቀጣይ ፈተና አሰጣጥ ልምድ የተወሰደበት መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ገልጸዋል፡፡ ሀላፊው አክለዉም ፈተናው በ45 የመፈተኛ ጣቢያዎች በ4 ዙር ለ30 ሺ የማህበራዊና የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች መሰጠቱን ጠቁመው በቀጣይ በልምምዱ የነበሩ ሁኔታዎችን በመገምገም ተማሪዎቹ ፈተናውን ያለምንም እንከን እንዲወስዱ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ የሚሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
ፈተናውን በበይነ መረብ የወሰዱ ተማሪዎች ለሁለት ቀናት ያደረጉት የልምምድ ፈተና ለዋናው ፈተና በአግባቡ እንዲዘጋጁ የሚያግዛቸው መሆኑን ለዝግጅት ክፍላችን በሰጡት አስተያየት አስታውቀዋል።
.