Announcement በከተማ አስተዳደሩ የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል

በከተማ አስተዳደሩ የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል

05th July, 2024

በከተማ አስተዳደሩ የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና እንዲካሄድ በቂ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት መከናወናቸው ተገለጸ።

(ሰኔ 25/2016 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በየደረጃው ከሚገኙ የከተማ አስተዳደሩ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ አመራሮች፣ ከአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን አመራሮችና መምሪያ ኃላፊዎች፣ ከፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ዘርፍ አመራሮች እንዲሁም ከደንብ ማስከበር ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች እና ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፕሬዘዳንቶች ጋር የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን ለማስፈጸም በተዘጋጀ የጸጥታ እቅድ ዙሪያ ውይይት አካሂዷል።

በከተማ አስተዳደሩ የሚሰጠው ብሔራዊ ፈተና ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲከናወኑ በየደረጃው የሚገኙ የጸጥታ መዋቅሩ አመራሮችና አባላት እያደረጉ ለሚገኘው የማይቋርጥ ድጋፍ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ምስጋና አቅርበው ዘንድሮ በአዲስ አበባ ከተማ ከዚህ በፊት ከነበረው አንጻር የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና መስጫ ጣቢያዎች ቁጥር በመጨመሩ ፈተናው በሁሉም ጣቢያዎች ከኩረጃ ነጻ ሆኖ ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲሰጥ ከጸጥታ አካላትና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ እንደሚሰራም አስታውቀዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሊዲያ ግርማ በከተማ አስተዳደሩ የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ያለምንም የጸጥታ ስጋትም ሆነ ሌሎች የፈተናውን ሂደት ከሚያውኩ ተግባራት ተጋላጭነት በጸዳ መልኩ እንዲካሄድ በቂ የቅድመ ዝግጅት ስራ መሰራቱን ገልጸዋል።

.

Copyright © All rights reserved.