በ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሥራና ተግባር ትምህርት (CTE) ተግባር ለማስፈፀም የተዘጋጀ ሰነድ ላይ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ::
(ታህሳሳ 2/2018 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሥርዓተ ትምህርት ማበልፀግና ትግበራ ዳይሬክቶሬት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሥራና ተግባር ትምህርትን ተግባር ለማስፈፀም የተዘጋጀ ሰነድ ላይ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል::
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዲናዖል ጫላ በስልጠናው መክፈቻ ባደረጉት ንግግር የተግባር ትምህርት በትምህርት ቤቶች የሚሰጥበትን ሁኔታ የተሻለ ለማድረግና ትምህርት ቤቶች በአካባቢያቸው ያሉ መልካም አጋጣሚዎችን በመጠቀም በቀላሉ ትምህርቱን ማማቻቸት የሚችሉበት መንገድ ላይ እውቀት የሚገኝበት ስልጠና እንደሆነ ተናግረዋል:: አቶ ዲናኦል አያይዘውም ትምህርትና ሥራና ክህሎት ቢሮዎች በቀጣይ የተግባር ላይ ትምህርትን ውጤታማ ለማድረግ እንዲችሉ እንዲሁም ስራውን ከኮሌጆች ጋር በማስተሳሰር ለመስራት ሊያካሂዱ የሚገባቸው ቅድመዝግጅት ስራዎች ላይ ግንዛቤ ይፈጥራል ብለዋል::
.