Home ቂርቆስ ፣ የካ እና ለሚ ኩራ ክፍለ ከተሞች በ2ኛው በከተማ አቀፍ ስፖርት ሊግ እና የመምህራን ስፖርታዊ ውድድር የቼስ ውድድርን በበላይነት አጠናቀቁ፡፡

ቂርቆስ ፣ የካ እና ለሚ ኩራ ክፍለ ከተሞች በ2ኛው በከተማ አቀፍ ስፖርት ሊግ እና የመምህራን ስፖርታዊ ውድድር የቼስ ውድድርን በበላይነት አጠናቀቁ፡፡

07th February, 2026

 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት እና ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮዎች በጋራ አዘጋጅነት እየተካሄደ በሚገኝው 2ኛው ከተማ አቀፍ የተማሪዎች ስፖርት ሊግ እና የመምህራን ስፖርታዊ ውድድር በቼስ ውድድር በመምህራን ቂርቆስ ክፍለ ከተማ፣ በሴት ተማሪዎች የካ እና በወንድ ተማሪዎች ለሚ ኩራ ክፍለ ከተሞች አሸናፊነት ተጠናቋል።

በመምህራን መካከል በተካሄደው ውድድር ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ብልጫ በመውሰድ የውድድሩ ሻምፒዮና መሆን ችሏል።

በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በሴ ተማሪዎች መካከል በተካሄደ ወሳኝ ጨዋታ የካ ክፍለ ከተማ በበላይነት ማጠናቀቅ የቻለ ሲሆን

ወንድ ተማሪዎች ባካሄዱት ማራኪ ውድድር ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የውድድሩ ሻምፒዮና ሆኗል፡፡

ዛሬ እዚህ ያየነው ተሰጥኦ የነገዋን ኢትዮጵያ በብልህነት የሚመሩ ወጣቶች መፍለቂያ መሆኑን ያሳየናል ያሉት የፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ እንዳልካቸው የቼስ ስፖርት በትምህርት ቤቶች ውስጥ በይበልጥ እንዲስፋፋ በትኩረት እንደሚሰራ አሳውቀዋል፡፡

በመምህራን መካከል በተካሄደው ውድድር ቂርቆስ ክፍለ ከተማን ተከትለው አቃቂ እና ቦሌ ክፍለ ከተሞች በቅደም ተከተል 2ኛ እና 3ኛ ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል፡፡

ጠንካራ ፉክክርን ያስተናገደው የሁለተኛ ደረጃ ሴት ተማሪዎች ውድድር ንፍስ ስልክ ክፍለ ከተማ የብር ሜዳልያ በመውሰድ 2ኛ ደረጃ ሲይዝ ጉለሌ ክፍለ ከተማ 3ኛ ሆኖ አጠናቋል፡፡

በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በወንዶች መካከል የተካሄደውን ውድድር የካ ክፍለ ከተማ የብር ሜዳልያ፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የነሐስ ሜዳልያ ባለቤት በመሆን አጠናቀዋል፡፡

.

Copyright © All rights reserved.