ትምህርቱ በሁሉም ክፍለከተሞች በተቋቋሙ የክላስተር ማዕከላት በየአቅራቢያው ከሚገኙ የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡ የ11ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ቅዳሜ ሙሉ ቀን የማስተማር ብቃታቸው ተሽለው በተመለመሉ መምህራን በመሰጠት ላይ ይገኛል።
በክላስተር ማዕከላቱ የሚማሩ ተማሪዎች ለብሔራዊ ፈተናው በአግባቡ ዝግጁ መሆን እንዲችሉ ከ9ኛ እስከ12ኛ ክፍል የሚሰጠው ትምህርት ተጨምቆ እንዲማሩ የተደረገ ሲሆን ስትራቴጂው በአግባቡ ተግባራዊ ሆኖ የሚፈለገው ውጤት እንዲመዘገብ ወላጆችን ጨምሮ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተገቢውን ድጋፍና ክትትል ማድረግ ይጠበቃል።
የዝግጅት ክፍላችን ምልከታ ባደረገባቸው በሽመልስ ሀብቴ ፣ በደራርቱ ቱሉ እና በኢትዮጃፓን 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ክላስተሮች የማጠናከሪያ ትምህርቱ ተጠናክሮ በመሰጠት ላይ ይገኛል።