Announcement የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤትን ለማላቅ የተዘጋጀውን የማላቅ ስትራቴጂ መሰረት በማድረግ ከሰኞ ጀምሮ ወደ ስራ እንዲገባ አቅጣጫ ተቀመጠ።

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤትን ለማላቅ የተዘጋጀውን የማላቅ ስትራቴጂ መሰረት በማድረግ ከሰኞ ጀምሮ ወደ ስራ እንዲገባ አቅጣጫ ተቀመጠ።

18th October, 2025

በውይይቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ስትራቴጂክ ካውንስል አባላት እና የክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች እንዲሁም ሁሉም የመንግስት እና የግል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህራን እና የ2ኛ ደረጃ ሱፐርቫይዘሮች የተሳተፉ ሲሆን የማላቅ ስትራቴጂው በዝርዝር ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በከተማ አስተዳደሩ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ውጤታማ እንዲሆን ቢሮው የተለያዩ ተግባራትን የያዘ ስትራቴጂ አዘጋጅቶ ለተግባራዊነቱ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ መሆኑን ገልጸዋል::

አያይዘውም ስትራቴጂውን በአግባቡ ተግባራዊ በማድረግ ውጤት ማስመዝገብ እንዲቻል የክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች የትምህርት ቤት ርዕሰ መምህራን እና የሚመለከታቸው አካላት የክላስተር ማዕከላትን በማደራጀት ፣ ተማሪዎችን በማስተባበርና ወላጆችን በማወያየት ለእቅዱ ውጤታማነት በጋራ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል። እንዲሁም  ከሰኞ ጀምሮም ወደ ስራ እንዲገባም አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

በውይይቱ የአጠቃላይ ትምህርት ሱፐርቪዥን ዳይሬክተር በሆኑት አቶ ጥላዬ ዘውዴ አማካኝነት በየክፍለ ከተማው የሚቋቋሙ ክላስተር ማዕከላት አደረጃጀትን ጨምሮ በስትራቴጂው የተቀመጡ ሌሎች የአፈፃፀም ተግባራትን በአግባቡ መተግበር  የሚያስችል የማላቅ ስትራቴጂው ለተሳታፊዎች ቀርቧል::

.

Copyright © All rights reserved.