በአዲስ አበባ የሚገኙ የትምህርት ማህበረሰብ “ትውልድ በመምህራን ይቀረፃል፤ሀገር በትምህርት ይበለፅጋል "በሚል መሪ ቃል በ11 ዱም ክ/ከተማ ሲያካሂዱት የነበረዉ ዉይይት መጠናቀቁ ተገለፀ::
(ግንቦት 7/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በመሪ ሃሳቡ ከመምህራንና ከትምህርት አመራሮች ጋር ለሁለት ቀናት በ 11 ዱም ክፍለ ከተሞች ሲያካሂደዉ የነበረዉን ዉይይት በዛሬዉ እለት በስኬት ተጠናቋል፡፡
የቢሮዉ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ እንደገለፁት በሁሉም ክ/ከተሞች ባሉ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚያስተምሩ መምህራንና የትምህርት አመራሮች በተሳተፉባቸዉ መድረኮች ነፃና ዲምክራሲያዊ የሆኑ ዉይይቶች መከናወናቸዉን ተናግረዋል፡፡
የዉይይቱን ዓላማ ሲገልፁም ትምህርት የብዙ ባለድርሻ አካላት ቁርጠኛነት እና እርብርብ የሚጠይቅ በመሆኑ ተቀናጅቶ በመስራት የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥና ዉጤትን ለማላቅ እንዲሁም በዘላቂነት የተሻለች ሃገርና ትዉልድን ለመገንባት ከምንም በላይ የማይተካ ሚና ያለዉ በመሆኑ ነዉ ብለዋል፡፡
አያይዘዉም ከትምህርት ማህበረሰብ ጋር መወያየት ማለት ስለሃገር፤ስለ ትዉልድ መወያየት መሆኑን ጠቁመዉ ከዚህ አኳያ ከማንም በላይ ትልቅ ሃላፊነት ያለብን መሆናችንን አዉቀን ታሪካዊ አደራችንን መወጣት ይጠበቅብናል ሲሉ ገልፀዋል::
.