የበጎ ፍቃድ ትምህርቱ ከተማ አስተዳደሩ በክረምት ወቅት የ90 ቀን እቅድ ውስጥ ተካቶ እድሜያቸው ከ15 አመት በላይ ለሆነ ወጣቶችና ጎልማሶች የተሰጠ ሲሆን በእቅዱ 11ሺ ጎልማ ሶችን ለማስተማር ታቅዶ 10,552 የሚሆኑት ትምህርቱን በአግባቡ ተከታትለው ማጠናቀቃቸውን ከልዩ ፍላጎትና ጎልማሶች መ ሰረታዊ ትምህርት ዳይሬክቶሬት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የልዩ ፍላጎትና ጎልማሶች መ ሰረታዊ ትምህርት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ገመቺስ ፍቃዱ በከተማ አስተዳደሩ በትምህርት ሴክተሩ በ90 ቀን ከታቀዱ የንቅናቄ ስራዎች መካከል ጎልማሶችን በክረምት የበጎ ፍቃድ መርሀግብር የትምህርት አገልግሎቱ ተጠቃሚ ማድረግ አንዱ መሆኑን ጠቁመው በመርሀግብሩ በአስራ አንዱ ክፍለከተሞች በሚገኙ የማስተማሪያ ጣቢያዎች 10,552 ጎልማሶች ትምህርቱን በአማርኛ እና አፋን ኦሮሞ ቋንቋዎች በአግባቡ ተከታትለው የብርሀን ምዘና መውሰዳቸውን አስታውቀዋል።
ዳይሬክተሩ አያይዘውም የብርሀን ምዘናውን ወስደው 50% እና በላይ ካስመዘገቡት መካከል የተወሰኑት በምርጫቸው መደበኛ ትምህርት በመማር ላይ መሆናቸውን እና ቀሪዎቹ በቀጣይ ቀናት ወደ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች በመግባት እንደፍላጎታቸው በመረጡት የሙያ መስክ የአጭር ጊዜ ስልጠና ወስደው ህይወታቸውን የሚመሩበት አማራጭ መቀመጡን ጠቁመው ትምህርቱ በስኬት እንዲጠናቀቅ በየደረጃው ድጋፍ ላደረጉ አመራሮች፣ባለሙያዎች እንዲሁም ለበጎ ፍቃደኛ ወጣቶችና አመቻቾች ምስጋና አቅርበዋል።
.