የልዩ ፍላጎት አካቶ ትምህርትና የጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት ትግበራ ዳይሬክቶሬት ከኮከበ ጽባህ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በልዩ ፍላጎት ትምህርት አሰጣጥ ላይ መሰረት ያደረገ ልምድ ልውውጥ አካሂዷል፡፡
የልዩ ፍላጎት አካቶ ትምህርትና የጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ገመቺስ ፈቃዱ በኮከበ ፅባህ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ልምድ ልውውጥ መካሄዱ የልዩ ፍላጎት ድጋፍ መስጫ ማእከል አደረጃጀት ፣ የመማር ማስተማር ሁኔታና በአካቶ ትምህርት እና በልዩ ክፍል ያሉትን ተማሪዎች በተሻለ የትምህርት ስርዓት ለማስተማር እየተደረገ ያለው ጥረት የተሻለ በመሆኑ ለሌሎች ልምድ የሚሰጥ መሆኑን ተናግረዋል::
አቶ ገመቺስ የልምድ ልውውጡ ተሳታፊዎች የልዩ ፍላጎት ተማሪዎች የፋይል አደረጃጀት ፣ የልዩ ፍላጎት ተማሪዎች የግብዓት አጠቃቀምና የልዩ ፍላጎት መማሪያ ቦታን ምቹ ማድረግ እንዲሁም መፀዳጃ ፣ ውሃ ፣ ራምፕ እና አቅጣጫ ማሳያን ምቹ ከማድረግ አንጻር የተሰሩ ስራዎችን አይተው በትምህርት ቤታቸው እንዲተገብሩ አቅጣጫ የሚሰጥ መሆኑን ተናግረዋል ፡፡ አያይዘውም የልዩ ፍላጎት ተማሪዎች የተሻለ ትምህርት ማስተማርና መንከባከብ ላይ ትኩረት አድርገው እንዲሰሩ ልምድ ልውውጡ ላይ አሳስበዋል፡፡

.