Announcement የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክ አገልግሎት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት በእድገት በህብርት ቅድመ 1ኛና አንደኛ መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የተለያዩ ድጋፎችን አደረገ።

የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክ አገልግሎት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት በእድገት በህብርት ቅድመ 1ኛና አንደኛ መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የተለያዩ ድጋፎችን አደረገ።

26th September, 2025

(መስከረም 15/2018 ዓ.ም) በትምህርት ቤቱ በመገኘት የማጣቃሻና አጋዥ መጽሀፍ ፣ የስፖርት ቁሳቁስ ፣ እንዲሁም የተለያዩ የሙዚቃ ክዋኔ ማስተማሪያ ግባቶችን ድጋፍ አድርገዋል።

በድጋፍ ስነ_ስራዓቱ ላይ የተገኙት የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰማኝ አስታጥቄ መንግስት ለትምህርት ሴክተሩ በሰጠው ልዩ ትኩረት ሰፊ ተግባራት እየተከናወነ ሲሆን በዚህም ሰፊ ለውጥ መምጣቱን አስታውቀዋል፤ በተለይም የተማሪ ውጤትና ስነ-ምግባር ሊያሻሽሉ የሚችሉ የተማሪዎች ምገባ፣ የተማሪዎች ሙሉ ግብአት አቅርቦት ፣ የትምህርት ቤቶች ግቢ ለመምህራን ፣ ለተማሪዎችና ለትምህርት ቤቱ ስታፍ ምቹና ማራኪ በማድረግ ፣ የትምህርት ውስጣዊ ብቃትን ሊያረጋግጡ የሚችሉ ስራዎች የተሰሩ ሲሆን በዚህም በነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድ ላይ ተጨባጭ ለውጥ መመዝገቡን ገልጸዋል።

.

Copyright © All rights reserved.