Notice-bg

የፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ምዝገባ ማስታወቂያ!

21 Aug 2025

የፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ምዝገባ ማስታወቂያ!

 የፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ምዝገባ ባለፉት ቀናት በኦንላይን ሲካሄድ መቆየቱ ይታወቃል ። ነገር ግን በተቀመጠው ጊዜ ገደብ ውስጥ የ8ኛ ክፍል ውጤት ያልደረሰላቸው በርካታ አካባቢዎች በመኖራቸው እንዲሁም በሌሎች ምክንያቶች ያልተመዘገቡ ተማሪዎች በመኖራቸው ምዝገባውን ለተወሰነ ጊዜ ማራዘም ማስፈለጉን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

በመሆኑም እስካሁን ያልተመዘገባችሁ ተማሪዎች ምዝገባ እስከ ነሃሴ 25/2017 ዓ.ም ድረስ የተራዘመ መሆኑን አውቃችሁ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

ማሳሰቢያ፦ምዝገባው እስከ ነሃሴ 25/2017 ዓ.ም ድረስ የሚከናውን ሲሆን: - 

የ6ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በ2015 የትምህርት ዘመን ያልወሰዳችሁ ተማሪዎች የክፍል ውጤታችሁንና ካርዳችሁን፤

8ኛ ክፍል በተመለከተ የምታስገቡት ውጤት የሚኒስትሪ ውጤታችሁን ሲሆን የሚኒስትሪ ካርድ ያልወሰዳችሁ ኦላይን 

ያለውን ውጤታችሁን ስካን አድርጋችሁ ማያያዝ ይጠበቅባችዋል፡፡

ከዚህ ቀደም የተመዘገባችሁ እና በትክክል ያላስገባችሁ ተማሪዎች በድጋሚ አስተካክለችሁ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን የተገለጸ ሲሆን ለመመዝገብ https://sbs.moe.gov.et/apply


Copyright © All rights reserved.