Notice-bg

የ8ተኛ ክፍል የሚኒስትሪ ውጤት ተለቀቀ

24 Jun 2025

የ8ተኛ ክፍል የሚኒስትሪ ውጤት ተለቀቀ

አዲስ አበባ ከተማ የ2017 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 88.8 % ያህሉ 50% እና ከዛ በላይ በማምጣት ወደ ቀጣዩ የክፍል ደረጃ መሸጋገራቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አሳውቋል። በመዲናዋ የ2017 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት ይፋ ተደርጓል። በ2017 ዓ.ም ፈተናውን ከወሰዱ 70,525 ተማሪዎች መካከል 88.8 በመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች 50% እና በላይ አስመዝግበው ወደ ቀጣዩ የክፍል ደረጃ መሸጋገራቸውን ይፋ አድርጓል።ዘንድሮው በከተማ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት ካስመዘገቡ 20 ተማሪዎች መካከል 13 የሚሆኑት በእቴጌ መነን የልጃገረዶች እና በገላን የወንዶች አዳሪ ትምህርት ቤቶች የተማሩ መሆናቸው ተገልጿል።የዘንድሮው ውጤት በ2016 ዓ.ም ከነበረው የ78.9% ወደ 88.8% ማደጉን በመግለጽ መምህራንን ጨምሮ በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላት ተማሪዎቹ ውጤታማ እንዲሆኑ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ቢሮው ምስጋና አቅርቧል።ተፈታኝ ተማሪዎች ከታች የተቀመጠውን ሊንክ በመጠቀም ከዛሬ ጀምሮ ውጤታቸውን ማየት እንደሚችሉ ተጠቁሟል።

ውጤት መመልከቻ ፦ https://aa.ministry.et/#/result

Copyright © All rights reserved.